የSpotify የግላዊነት መመሪያ
ከ10ኦክቶበር 2024ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል
2. የእርስዎ የግል ውሂብ መብቶች እና ቁጥጥሮች
4. የእርስዎን የግል ውሂብ የምንጠቀምበት ዓላማ
1. ስለዚህ መመሪያ
ይህ መመሪያ በSpotify AB ላይ የግል ውሂብዎን እንዴት እንደምናስሄድ ይገልጻል።
እንደ ተጠቃሚ በሁሉም የSpotify የዥረት አገልግሎቶች
- አጠቃቀምዎ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። ለምሳሌ ይህ የሚከተሉትን ያካትታል፦
- በማንኛውም መሳሪያ ላይ Spotifyን መጠቀምዎን
- የእርስዎ የተጠቃሚ ተሞክሮን ግላዊነት ማላበስን
- አገልግሎታችንን ለማቅረብ የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶችን
- የእርስዎ የSpotify መለያ ከሌላ መተግበሪያ ጋር ያለውን ግንኙነት
- ሁለቱም የእኛ ነፃ ወይም የሚከፈልባቸው የዥረት አማራጮችን (እያንዳንዱ << የአገልግሎት አማራጭ ነው >>)
- ሌሎች የዚህን የግላዊነት መመሪያ አገናኝ የሚያካትቱ የSpotify አገልግሎቶችን። እነዚህ የSpotify ድረገጾችን፣ የደንበኞች አገልግሎትን እና የማህበረሰብ ጣቢያን ያካትታሉ
ከአሁን ጀምሮ፣ እነዚህን << የSpotify አገልግሎት ብለን እንጠራቸዋለን>>።
በየጊዜው አዲስ ወይም ተጨማሪ አቅርቦቶችን ልንገነባ እንችላለን። ስናስተዋውቃቸው በሌላ መልኩ ካልተገለጸ በስተቀር እነሱም ለዚህ መመሪያ ተገዢ ይሆናሉ።
ይህ መመሪያ የሚከተለው አይደለም ...
- የSpotify የአገልግሎት ውል፣ ይህም የተለየ ሰነድ ነው። የአገልግሎት ውል የSpotify አገልግሎትን ለመጠቀም በእርስዎ እና በSpotify መካከል ያለውን ህጋዊ ውል ይዘረዝራል። እንዲሁም የSpotify ደንቦችን እና
- የራሳቸው የግላዊነት መመሪያ ስላላቸው ሌሎች የSpotify አገልግሎቶች አጠቃቀምዎ የተጠቃሚ መብቶችዎን ይገልፃል። ሌሎች የSpotify አገልግሎቶች Anchorን፣ Soundtrapን፣ Megaphoneን እና Spotify Live መተግበሪያን ያካትታሉ
ሌሎች ምንጮች እና ቅንብሮች
ስለ የግል ውሂብዎ ቁልፍ መረጃ እዚህ መመሪያ ውስጥ አለ። ሆኖም፣ የእኛን ሌሎች የግላዊነት ምንጮችን እና ቁጥጥሮችን መመልከት ይፈልጉ ይሆናል፦
- የግላዊነት ማዕከል፦ቁልፍ የርዕሶች ማጠቃለያ ያለው ለተጠቃሚ ተስማሚ የሆነ ማዕከል።
- የመለያ ግላዊነት: የተስማማ ማስታወቂያን ጨምሮ የተወሰኑ የግል መረጃዎችን ሂደት ይቆጣጠሩ ።
- የማሳወቂያ ቅንብሮች፦ ከSpotify የትኞቹን የግብይት ግንኙነቶች እንደሚያገኙ ያቀናብሩ።
- (በSpotify የዴስክቶፕ እና የሞባይል ስሪቶች ላይ የሚገኙ) ቅንብሮች፦ እንደ << ማህበራዊ >> ወይም << ይፋ ይዘት >> ያሉ የተወሰኑ የSpotify አገልግሎትን ይቆጣጠራሉ። በ << ማህበራዊ >> ቅንብር ላይ፣ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
- የግል ክፍለጊዜ መጀመር
- በSpotify ላይ የሚያዳምጡትን ለተከታዮችዎ ያጋሩ እንደሆነ መምረጥ
- የእርስዎን በቅርብ ጊዜ የተጫወቱትን አርቲስቶች በይፋዊ መገለጫዎ ላይ ያሳዩ እንደሆነ መምረጥ
በ<< ይፋ ይዘት >> ቅንብር ላይ ይፋ ደረጃ የተሰጠው ይዘት የSpotify መለያዎ ላይ መጫወት ይችል እንደሆነ መቆጣጠር ይችላሉ።
- የኩኪዎች ፖሊሲ ፦ ኩኪዎችን እንዴት እንደምንጠቀም እና የኩኪ ምርጫዎችን እንዴት ማስተዳደር እንደምንችል አስመልክቶ መረጃ። ኩኪዎች አንድ ድር ጣቢያን ሲጎበኙ በስልክዎ፣ ጡባዊዎ ወይም ኮምፒውተርዎ ላይ የሚቀመጡ ፋይሎች ናቸው።
2. የእርስዎ የግል ውሂብ መብቶች እና ቁጥጥሮች
ብዙ የግላዊነት ህጎች ለግለሰቦች በግል ውሂባቸው ላይ መብቶችን ይሰጣሉ። እነዚህ ህጎች አጠቃላይ የውሂብ ጥበቃ ደንብ፣ ወይም <>ን ያካትታሉ።
አንዳንድ መብቶች የሚተገበሩት Spotify የእርስዎን ውሂብ ለማሰናዳት የተወሰነ << ህጋዊ መሰረት >> ሲጠቀም ብቻ ነው። እያንዳንዱን ህጋዊ መሰረት እናብራራለን እና Spotify እያንዳንዱን ሲጠቀም፣ በክፍል 4 << የእርስዎን የግል ውሂብ የመጠቀም አላማችንን >> እንገልፃለን ።
ከዚህ በታች ያለው ሰንጠረዥ የሚከተሉትን ያብራራል፦
- የእርስዎን መብቶች
- በሚተገበሩበት ጊዜ ያሉ ሁኔታዎችን (እንደ አስፈላጊው ሕጋዊ መሠረት ያለ)
- እነሱን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል
የሚከተሉትን ማድረግ መብትዎ ነው... |
እንዴት?
|
|
---|---|---|
መረጃ ይኑርዎት |
ስለእርስዎ ስለምናስሄደው የግል ውሂብዎ እና እንዴት እንደምናሄደው መረጃ ይኑርዎት። |
የምናሳውቅዎት፦
|
መዳረሻ |
እኛ ስለእርስዎ የምናስሄደውን የግል ውሂብ መዳረሻ ይጠይቁ። |
ከSpotify የእርስዎን የግል ውሂብ ቅጂ ለመጠየቅ፣ ከሚከተሉት አንዱን ያድርጉ፦
ውሂብዎን ሲያወርዱ Spotify በGDPR አንቀጽ 15 መሰረት ማቅረብ ያለበት የውሂብዎ መረጃ ይደርስዎታል። የእርስዎን የግል ውሂብ እንዴት እንደምናስሄድ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ እኛን ማነጋገር ይችላሉ። |
እርማት |
የግል ውሂብዎ ትክክል ካልሆነ ወይም ካልተሟላ እንድናሻሽለው ወይም እንድናዘምነው ይጠይቁ። |
የእርስዎን የተጠቃሚ ውሂብ በመለያዎ ውስጥ «መገለጫ አርትዕ» በሚለው ስር ወይምእኛን በማነጋገር ማርትዕ ይችላሉ ። |
መደምሰስ |
የተወሰነውን የግል ውሂብዎን እንድንሰርዝ ይጠይቁ። ለምሳሌ፣ የሚከተለውን ዓይነት የግል ውሂብ እንድንሰርዝ ሊጠይቁን ይችላሉ፦
Spotify የእርስዎን ውሂብ መሰረዝ የማይችልባቸው ሁኔታዎች አሉ፣ ለምሳሌ፦
|
ከSpotify ላይ የግል ውሂብን ማጥፋት የሚችሉባቸው በርካታ መንገዶች አሉ፦
|
ገደብ |
ሁሉንም ወይም የተወሰነ የግል ውሂብዎን ማስሄድ እንድናቆም ይጠይቁ። የሚከተሉት ከሆኑ ይህን ማድረግ ይችላሉ፦
ይህን ሂደት ለጊዜው ወይም በቋሚነት እንድናቆም መጠየቅ ይችላሉ። |
እኛን በማነጋገርየመገደብ መብትዎን መጠቀም ይችላሉ። |
ይቃወሙ |
የእርስዎን የግል ውሂብ እንዳናሰናዳ ይቃወሙ። የሚከተሉት ከሆኑ ይህን ማድረግ ይችላሉ፦
|
የመቃወም መብትዎን ለመጠቀም የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
|
የውሂብ ተንቀሳቃሽነት |
የእርስዎን የግል ውሂብ ቅጂ በኤሌክትሮኒክ ቅርጸት እና ያንን የግል መረጃ ለሌላ ወገን አገልግሎት ለመጠቀም የማስተላለፍ መብትን ይጠይቁ። በፈቃደኝነት ሕጋዊ መሰረት ወይም በውል አፈጻጸም ላይ የእርስዎን የግል መረጃ በምንናሰናዳበት ጊዜ ውሂብዎን እንድናስተላልፍ ሊጠይቁን ይችላሉ። ሆኖም Spotify በተቻለ መጠን ማንኛውንም ጥያቄ ለማክበር ይሞክራል። |
የተንቀሳቃሽነት መብትን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል መረጃ ለማግኘት ከላይ ያለውን «መዳረሻ»ን ይመልከቱ። |
ለራስ-ሰር የውሳኔ አሰጣጥ ተገዢ አለመሆን |
በራስ ሰር ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ብቻ (የሰው ተሳትፎ የሌለባቸው ውሳኔዎች) ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ተገዢ መሆን የለብዎትም፣ መገለጫ ምዘናን ጨምሮ፣ ውሳኔው በእርስዎ ላይ ሕጋዊ ተጽእኖ ይኖረዋል ወይም ተመሳሳይ ጉልህ ውጤት ያመጣል። |
Spotify በSpotify አገልግሎት ውስጥ ይህን ዓይነት የራስ ሰር ውሳኔ አይሰጥም። |
ፈቃደኝነትን መተው |
የእርስዎን የግል ውሂብ እንድንሰበስብ ወይም እንድንጠቀም የሰጡትን ፈቃደኝነትዎን ያንሱ። Spotify የእርስዎን የግል ውሂብ በፈቃደኝነትሕጋዊ መሰረት ላይ እያሰናዳ ከሆነ ይህን ማድረግ ይችላሉ። |
ፈቃደኝነትዎን ለመተው፣ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
|
ቅሬታ የማቅረብ መብት |
ለማናቸውም ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች የስዊድን የግላዊነት ጥበቃ ባለስልጣንን ወይም አካባቢያዊ የውሂብ ጥበቃ ባለስልጣንን ያነጋግሩ። |
የስዊድን ባለስልጣን አድራሻን እዚህ ማግኘት ይችላሉ። እንዲሁም ወደ የእርስዎ አካባቢያዊ የውሂብ ጥበቃ ባለስልጣን ድር ጣቢያ መሄድ ይችላሉ። |
የተስማሙ ማስታወቂያ መቆጣጠሪያዎች
የተስማማ ማስታወቂያ ምንድን ነው?
- ይህ ለእርስዎ ይበልጥ ተዛማጅ እንዲሆኑ ለማድረግ ማስታወቂያዎች ለመንደፍ የእርስዎን መረጃ ስንጠቀም ነው። እንዲሁም ይህ በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ማስታወቂያ በመባል ይታወቃል።
- የተስማማ ማስታወቂያ ምሳሌ አንድ የማስታወቂያ አጋር መኪና እንደሚወዱ የሚጠቁም መረጃ ሲኖረው ነው። ይህ ስለ መኪናዎች ማስታወቂያዎችን እንድናሳይዎት ያስችለናል።
የተስማሙ ማስታወቂያዎችን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል፦
- <<የተስማሙ ማስታወቂያዎች>> ከሚለው ስርየመለያ ግላዊነትገፅዎ ላይ የተስማማ ማስታወቂያን መቆጣጠር ይችላሉ።
- እንዲሁም ለአንዳንድ ፖድካስቶች የተስማሙ ማስታወቂያዎችን በክፍል ትርዒት መግለጫ ውስጥ ያለውን አገናኝ በመጠቀም መቆጣጠር ይችላሉ። ይህ የይዘት አቅራቢው እሱን ፈንድ ለማድረግ በፖድካስት ውስጥ ማስታወቂያውን ሲያስገባ ተፈጻሚ ይሆናል። Spotify ላይሆን የሚችለው አዘጋጅ አቅራቢው፣ እነዚህን መቆጣጠሪያዎች ለፖድካስቱ ያስተዳድራል።
የመለያ ግላዊነት ገፅዎ ላይ ከተበጁ ማስታወቂያዎች <<መርጠው ከወጡ>> አሁንም ማስታወቂያ ሊያገኙ ይችላሉ። ይህ በነፃ የአገልግሎት ምርጫችን ላይ፣ እንዲሁም የእኛን የሚከፈልበት የአገልግሎት አማራጭን፣ እንደ አስፈላጊነቱ (ለምሳሌ በፖድካስቶች ውስጥ ያሉ ማስታወቂያዎችን) ሊያካትት ይችላል። እንዲህ ዓይነት ማስታወቂያ በእርስዎ የምዝገባ መረጃ እና አሁን በአገልግሎታችን ላይ በሚያዳምጡት ነገር ላይ የተመሰረተ ነው። ለምሳሌ፣ የምግብ ማብሰል ፖድካስት እየሰሙ ከሆነ፣ የምግብ አሰናጅ ማስታወቂያ ሊሰሙ ይችላሉ።
3. ስለእርስዎ የምንሰበስበው የግል መረጃ
እነዚህ ሠንጠረዦች ከእርስዎ የምንሰበስበውን የግል ውሂብ ምድቦችን ያዘጋጃሉ።
ለSpotify አገልግሎት ሲመዘገቡ
ወይም መለያዎን ሲያዘምኑ የሚሰበሰብ
|
|
---|---|
ምድብ |
መግለጫ |
የተጠቃሚ ውሂብ |
የSpotify መለያዎን ለመፍጠር የሚያስፈልገን እና የSpotify አገልግሎትን ለመጠቀም የሚያስችልዎት የግል መረጃ። የሚሰበሰበው እና ጥቅም ላይ የሚውለው የውሂብ አይነት እርስዎ ባለዎት የአገልግሎት አማራጭ ይወሰናል። እንዲሁም መለያዎን በሚፈጥሩበት መንገድ፣ ባሉበት ሀገር እና ለመግባት የሦስተኛ ወገን አገልግሎቶችን ይጠቀሙ እንደሆነ ላይ ይወሰናል። ይህ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦
ከእነዚህ ውሂቦች የተወሰነውን ከእርስዎ እንቀበላለን ለምሳሌ፣ ከመመዝገቢያ ቅጽ ወይም ከመለያ ገጽ። እንዲሁም የተወሰነ ውሂብ ከመሣሪያዎ እንሰበስባለን ለምሳሌ ሀገር ወይም ክልል። ይህን ውሂብ እንዴት እንደምንሰበስብ እና እንደምንጠቀመው የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ በአጠቃቀም የውሂብ ምድብ ውስጥ «የእርስዎን አጠቃላይ (ትክክለኛ ያልሆነ) አካባቢ» ይመልከቱ። |
የጎዳና አድራሻ ውሂብ |
በሚከተሉት ምክንያቶች የጎዳና አድራሻዎን ልንጠይቅዎ እና ልናሄደው እንችላለን፦
በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ አድራሻዎን እንዲያረጋግጡ ለማገዝ እንደ Google ካርታዎች ያለ የሦስተኛ ወገን መተግበሪያን ልንጠቀም እንችላለን። |
በእርስዎ የSpotify አገልግሎት አጠቃቀም በኩል የተሰበሰበ | |
---|---|
ምድቦች |
መግለጫ |
የአጠቃቀም ውሂብ |
የSpotify አገልግሎትን ሲደርሱ ወይም ሲጠቀሙ ስለእርስዎ የተሰበሰበ እና የተሰናዳ የግል መረጃ። ይህ የሚያካትተው ጥቂት የመረጃ ዓይነቶች በሚከተሉት ክፍሎች ውስጥ ተዘርዝረዋል። Spotifyን እንዴት እንደሚጠቀሙ መረጃ ምሳሌዎቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
የእርስዎ የቴክኒክ ውሂብ ምሳሌዎቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
የእርስዎ አጠቃላይ (ትክክለኛ ያልሆነ) አካባቢ የእርስዎ አጠቃላይ አካባቢ አገር፣ ክልል ወይም ግዛትን ያካትታል። ይህን ከቴክኒካዊ መረጃ ልንማር እንችላለን (ለምሳሌ፣ የእርስዎ አይፒ አድራሻ፣ የመሣሪያዎ ቋንቋ ቅንብሮች) ወይም የክፍያ ምንዛሬ። ይህ የሚከተሉትን ለማድረግ ያስፈልገናል፦
የእርስዎ መሣሪያ ዳሳሽ ውሂብ ይህ ውሂብ የሚያስፈልጋቸው የSpotify አገልግሎት ባህሪያትን ለማቅረብ አስፈላጊ ከሆነ በእንቅስቃሴ የመነጨ ወይም በአቅጣጫ የመነጨ የመሣሪያ ዳሳሽ ውሂብ። ይህ መሣሪያዎን የሚያንቀሳቅሱበትን ወይም የሚይዙበትን መንገድ መሣሪያዎ የሚሰበስበው ውሂብ ነው። |
እርስዎ ለመስጠት ሊመርጡ የሚችሉት ተጨማሪ ውሂብ | |
---|---|
ምድቦች |
መግለጫ |
የድምጽ ውሂብ |
የድምጽ ባህሪያት በገበያዎ ውስጥ የሚገኙ ከሆነ እና የድምጽ ባህሪን ለመጠቀም በመረጡበት ጊዜ የድምጽ ውሂብን እንሰበስባለን እና እናሰናዳለን። የድምጽ ውሂብ ማለት የድምጽዎ የኦዲዮ ቅጂዎች እና የእነዚህ ቅጂዎች የጽሑፍ ግልባጮች ማለት ነው። የተለያዩ የድምጽ ባህሪያት እንዴት እንደሚሰሩ እና እንዴት እነሱን መቆጣጠር እና ማጥፋት እንደሚችሉ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የእኛን የድምጽ መቆጣጠሪያ መመሪያ ይመልከቱ ። |
የክፍያ እና የግዢ ውሂብ |
ከSpotify ማንኛውንም ግዢ ከፈጸሙ ወይም ለሚከፈልበት የአገልግሎት አማራጭ ወይም ለሙከራ ከተመዘገቡ፣ የክፍያ ውሂብዎን ማሰናዳት አለብን። የተሰበሰው እና ጥቅም ላይ የዋለው ትክክለኛ የግል መረጃ እንደ በመክፈያ መንገድ መሰረት ይለያያል። እንደሚከተሉት ያሉ መረጃዎችን ያካትታል፦
|
የዳሰሳ ጥናት እና የምርምር ውሂብ |
ለዳሰሳ ጥናት ምላሽ ሲሰጡ ወይም በተጠቃሚዎች ምርምር ላይ ሲሳተፉ፣ ያቀረቡትን የግል መረጃ እንሰበስባለን እና እንጠቀማለን። |
ከላይ የተጠቀሱትን አንዳንድ መረጃዎች ከሦስተኛ ወገኖች እንቀበላለን። ከታች ያለው ሰንጠረዥ የሦስተኛ ወገን ምድቦችን ይገልፃል።
የእርስዎን ውሂብ የምንቀበልባቸው የሦስተኛ ወገን ምንጮች | ||
---|---|---|
የሦስተኛ ወገን ምድቦች |
መግለጫ |
የውሂብ ምድቦች |
የማረጋገጫ አጋሮች |
ሌላ አገልግሎት ተጠቅመው ለSpotify አገልግሎት ከተመዘገቡ ወይም ከገቡ ይህ አገልግሎት መረጃዎን ይልካል። ይህ መረጃ መለያዎን ከእኛ ጋር ለመፍጠር ይረዳል። |
የተጠቃሚ ውሂብ |
ከSpotify መለያዎ ጋር የሚያገናኟቸው የሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎች፣ አገልግሎቶች እና መሣሪያዎች |
የSpotify መለያዎን ከሦስተኛ ወገን መተግበሪያ፣ አገልግሎት ወይም መሣሪያ ጋር ካገናኙት ከእነሱ መረጃ ልንሰበስብ እና ልንጠቀም እንችላለን። ይህ ስብስብ ውህደቱን የሚቻል ለማድረግ ነው። እነዚህ የሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎች፣ አገልግሎቶች ወይም መሣሪያዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦
መረጃዎን ከተወሰኑ የሦስተኛ ወገኖች ከመሰብሰባችን በፊት ፈቃድዎን እንጠይቃለን። |
የተጠቃሚ ውሂብ የአጠቃቀም ውሂብ |
የቴክኒክ አገልግሎት አጋሮች |
የተወሰነ ውሂብ ከሚሰጡን የቴክኒክ አገልግሎት አጋሮች ጋር እንሰራለን። ይህ የአይፒ አድራሻዎችን ትክክለኛ ወዳልሆነ የአካባቢ ውሂብ (ለምሳሌ፣ ሃገር ወይም ክልል፣ ከተማ፣ ግዛት) ካርታ መስራትን ያካትታል። ይህ Spotify የSpotify አገልግሎትን፣ ይዘትን እና ባህሪያትን ማቅረብ እንዲችል ያደርገዋል። የተጠቃሚ መለያዎችን ለመጠበቅ ከሚያግዙን ከደህንነት አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር አብረን እንሰራለን። |
የተጠቃሚ ውሂብ የአጠቃቀም ውሂብ |
የክፍያ አጋሮች እና ነጋዴዎች |
በሦስተኛ ወገኖች በኩል ለመክፈል ከመረጡ (ለምሳሌ፣ ከስልክ ኩባንያ አቅራቢዎች) ወይም በክፍያ መጠየቂያ፣ ከክፍያ አጋሮቻችን መረጃ ልናገኝ እንችላለን። ይህ የሚከተሉትን ለማድረግ ያስችለናል፦
ወደ ነጋዴ ከመራንዎት፣ ከግዢዎ ጋር የተያያዘ መረጃን ከነጋዴው እንቀበላለን። ለምሳሌ፣ በሦስተኛ ወገን መድረክ ላይ ወዳለ የአርቲስት ሸቀጥ መደብር ወይም ወደ የሦስተኛ ወገን ትኬት መቁረጫ ድረ ገጽ ልንመራዎት እንችላለን። ይህን ውሂብ መቀበል የሚከተሉትን ለማድረግ ያስችለናል፦
|
የክፍያ እና የግዢ ውሂብ |
የማስታወቂያ እና የግብይት አጋሮች |
ከተወሰኑ የማስታወቂያ ወይም የግብይት አጋሮች ማጣቀሻዎችን እንቀበላለን። እነዚህ ማጣቀሻዎች አጋሮች ስለእርስዎ ፍላጎቶች እና ምርጫዎች ያሏቸው ግንዛቤዎች ናቸው። ይህ ይበልጥ ተዛማጅነት ያላቸውን ማስታወቂያዎች እና ግብይትን ለማቅረብ ያስችለናል። |
የአጠቃቀም ውሂብ |
የተገዙ ኩባንያዎች |
ከገዛናቸው ኩባንያዎች ስለእርስዎ መረጃ ልንቀበል እንችላለን። ይህ የእኛን አገልግሎቶች፣ ምርቶች እና አቅርቦቶች ለማሻሻል ነው። |
የተጠቃሚ ውሂብ የአጠቃቀም ውሂብ |
የSpotify የሞባይል መተግበሪያን ካወረዱ እና የወጥቶ የተጠቃሚ ተሞክሮን ተጠቅመው Spotifyን ለመጠቀም ከሞከሩ፣ የአጠቃቀም ውሂብን ጨምሮ ስለ Spotify አገልግሎት አጠቃቀምዎ የተገደበ መረጃ እንሰበስባለን። ይህንን የምናደርገው እርስዎ አገልግሎቱን እንዴት እንደሚደርሱ እና እንደሚጠቀሙ ለመረዳት ነው። እንዲሁም ይህን የምናደርገው ለእርስዎ ትክክለኛውን ተሞክሮ እንደምናቀርብ ለማረጋገጥ ነው፣ ለምሳሌ በአገርዎ ወይም በክልልዎ መሰረት። ሙሉ በሙሉ የአገልግሎታችንን ተሞክሮ ለማግኘት የSpotify መለያ ለመፍጠር ከወሰኑ ይህን ውሂብ ከእርስዎ የSpotify መለያ ውሂብ ጋር እናደባልቃለን።
4. የእርስዎን የግል ውሂብ የምንጠቀምበት ዓላማ
ከዚህ በታች ያለው ሰንጠረዥ የሚከተሉትን ያብራራል፦
- የግል ውሂብዎን የማሰናዳት ዓላማችን
- በመረጃ ጥበቃ ሕግ መሰረት ለእያንዳንዱ ዓላማ (እያንዳንዳቸው << ሕጋዊ መሰረት >>ተብለው የሚጠሩትን የእኛን የሕግ ማረጋገጫዎች)
- ለእያንዳንዱ ዓላማ የምንጠቀምባቸው የግል ውሂብ ምድቦች። ስለእነዚህ ምድቦች በክፍል 3 <<ስለእርስዎ የምንሰበስበው የግል መረጃ>> ውስጥ የበለጠ ይመልከቱ
ሠንጠረዡን ለመረዳት እንዲረዳዎ የእያንዳንዱ << ሕጋዊ መሰረት >> አጠቃላይ ማብራሪያ እነሆ፦
- የውል አፈጻጸም፦ የሚከተለውን ለማድረግ Spotify (ወይም ሦስተኛ ወገን) የእርስዎን የግል ውሂብ ማካሄዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፦
- ከእርስዎ ጋር በተደረገው ውል ውስጥ ያሉትን ግዴታዎች ለማክበር። ይህ የSpotify አገልግሎትን ለእርስዎ ለማቅረብ በአጠቃቀም ውል ስር ያሉ የSpotify ግዴታዎችን፣ ወይም
- ከእርስዎ ጋር አዲስ ውል ከመጀመሩ በፊት መረጃ ማረጋገጥን ያካትታት።.
- ሕጋዊ****ፍላጎት፦Spotify ወይም ሦስተኛ ወገን የግል ውሂብዎን በተወሰነ መንገድ የመጠቀም ፍላጎት ሲኖራቸው፣ ይህም ለእርስዎ እና ለሌሎች የSpotify ተጠቃሚዎች ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ግምት ውስጥ በማስገባት አስፈላጊ እና ትክክለኛ ነው። ለምሳሌ፣ ለሁሉም ተጠቃሚዎች የSpotify አገልግሎትን ለማሻሻል የእርስዎን የአጠቃቀም ውሂብ መጠቀም።አንድ የተወሰነ ምክንያት ለመረዳት ከፈለጉያነጋግሩን።
- ፈቃደኝነት፦Spotify የግል ውሂብዎን ለተወሰነ ዓላማ ለመጠቀም ስምምነትዎን በንቃት እንዲጠቁሙ ሲጠይቅዎት።
- የሕግ ግዴታዎችን ማክበር፦Spotify ሕግን ለማክበር የእርስዎን የግል ውሂብ ማስሄድ ሲኖርበት።
የእርስዎን ውሂብ የማሰናዳት ዓላማ
|
ዓላማውን የሚፈቅድ ሕጋዊ መሠረት
|
ለዚሁ ዓላማ ጥቅም ላይ የዋሉ የግል መረጃ ምድቦች
|
---|---|---|
ከእርስዎ ጋር ባለን ውል መሰረት የSpotify አገልግሎትን ለማቅረብ። የSpotify አገልግሎት ለምሳሌ፣ የግል ውሂብዎን የሚከተሉትን ለማድረግ ስንጠቀም፦
|
የውል አፈፃፀም |
|
ተጨማሪ የSpotify አገልግሎት ክፍሎችን ለማቅረብ። ለምሳሌ፣ ወደ Spotify ይዘት የሚወስድ አገናኝ ከሌላ ሰው ጋር እንዲያጋሩ ለማስቻል የእርስዎን የግል ውሂብ ስንጠቀም። |
ሕጋዊ ፍላጎት እዚህ የእኛ ሕጋዊ ፍላጎቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
|
|
የSpotify አገልግሎቱን አንዳንድ ተጨማሪ የበጎ ፈቃድ ባህሪያትን ለማቅረብ። ጉዳዩ ይህ ሲሆን፣ ፈቃደኝነትዎን በግልፅ እንጠይቃለን። |
ፈቃደኝነት |
|
በSpotify አገልግሎት ችግሮችን ለመመርመር፣ መላ ለመፈለግ እና ለመጠገን። |
የውል አፈፃፀም |
|
በSpotify አገልግሎት ላይ አዳዲስ ባህሪያትን፣ ቴክኖሎጂዎችን እና ማሻሻያዎችን ለመገምገም እና ለማዳበር። ለምሳሌ፦
|
ሕጋዊ ፍላጎት ሕጋዊ ፍላጎቶቻችን ለተጠቃሚዎቻችን ምርቶችን እና ባህሪያትን ማዘጋጀትን እና ማሻሻልን ያካትታሉ። |
|
ፈቃድዎን እንድንሰበስብ ሕጉ በሚያስገድድበት ለገበያ ወይም ለማስታወቂያ። ለምሳሌ፣ ፍላጎቶችዎን ለመረዳት ኩኪዎችን ስንጠቀም ወይም ሕጉ ለኢሜይል ግብይት ፈቃደኝነትን ሲጠይቅ። |
ፈቃደኝነት |
|
ሕጉ ፈቃደኝነትን ለማይፈልግበት ለሌላ ግብይት፣ ማስተዋወቂያ እና ማስታወቂያ ዓላማዎች። ለምሳሌ፣ ከፍላጎቶችዎ ጋር ለማስማማት ማስታወቂያን ለመንደፍ የእርስዎን የግል ውሂብ ስንጠቀም። |
ሕጋዊ ፍላጎት እዚህ ጋር ሕጋዊ ፍላጎቶቻችን ለSpotify አገልግሎት የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ማስታወቂያ መጠቀምን ያካትታሉ፣ በዚህም አብዛኛው በነጻ ማቅረብ እንችላለን። |
|
ተገዢ መሆን ላለብን ሕጋዊ ግዴታ ለማገዛት። ይህ ምናልባት የሚከተሉትን ሊሆን ይችላል፦
ለምሳሌ፣ ለዕድሜ ማረጋገጫ ዓላማዎች በሚፈለግበት ጊዜ የልደት ቀንዎን ስንጠቀም። |
የሕግ ግዴታዎችን ማክበር |
|
ከሕግ አስከባሪ አካላት፣ ፍርድ ቤቶች ወይም ሌሎች ስልጣን ያላቸው ባለስልጣናት የቀረበውን ጥያቄ ለማክበር። |
የሕግ ግዴታዎችን እና ሕጋዊ ፍላጎቶችን ማክበር የእኛ ሕጋዊ ፍላጎቶች የሕግ አስከባሪ ባለስልጣናትን ከባድ ወንጀል ለመከላከል ወይም ለመለየት ማገዝን ያካትታል። |
|
ከሦስተኛ ወገኖች ጋር የውል ግዴታዎችን ለመወጣት ለምሳሌ፣ ይህን ለማድረግ ከSpotify የመብት ባለቤት ጋር ስምምነት ስላለን ስለተጠቃሚዎቻችን ማዳመጥ ለዪ መረጃው የተደበቀ ውሂብን ስናቀርብ። |
ሕጋዊ ፍላጎት እዚህ የእኛ ሕጋዊ ፍላጎቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
|
|
የአእምሯዊ ንብረት ጥሰት እና አግባብነት የሌለው ይዘት ሪፖርቶች ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ። |
ሕጋዊ ፍላጎት የእኛ ሕጋዊ ፍላጎቶች የአዕምሮ ንብረት እና ዋናውን ይዘት መጠበቅን ያካትታሉ። |
|
ሕጋዊ የይገባኛል ጥያቄዎችን ለመመስረት፣ ለመለማመድ ወይም ለመከላከል። ለምሳሌ፣ በፍርድ ቤት ሙግት ውስጥ ከተሳተፍን ከዛ የሕግ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ለጠበቆቻችን መረጃ መስጠት አለብን። |
ሕጋዊ ፍላጎት እዚህ የእኛ ሕጋዊ ፍላጎቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
|
|
ለንግድ ሥራ እቅድ ማውጣትን፣ ሪፖርት ማድረግን እና ትንበያዎችን ለማካሄድ። ለምሳሌ፣ ምርቶቻችንን እና ባህሪያትን የምናስጀምርበትን አዲስ ቦታ ለማቀድ እንደ በሀገር ውስጥ ያሉ አዲስ የተመዝጋቢዎች ብዛት ያለ የተዋሃደ የተጠቃሚ ውሂብን ስንመለከት። |
ሕጋዊ ፍላጎት እዚህ ላይ ያሉት ሕጋዊ ፍላጎቶቻችን ለተጠቃሚዎቻችን ምርቶችን እና ባህሪያትን መመርመርን እና ማቀድን ያካትታሉ። |
|
ክፍያዎን ለማሰናዳት። ለምሳሌ፣ የSpotify ምዝገባን እንዲገዙ ለማስቻል የእርስዎን የግል ውሂብ ስንጠቀም። |
የውል አፈፃፀም እና ፈቃደኝነት |
|
የSpotify አገልግሎትን ደህንነቱ እንደተጠበቀ ለማቆየት እና ማጭበርበርን ለመለየት እና ለመከላከል። ለምሳሌ፣ የSpotify አገልግሎቱ በተጭበረበረ ሁኔታ መጠቀምን ለመፈተሽ የአጠቃቀም ውሂብን ስንመረምር። |
ሕጋዊ ፍላጎት እዚህ ላይ ያሉት ሕጋዊ ፍላጎቶቻችን የSpotify አገልግሎትን እና ተጠቃሚዎቻችንን ከማጭበርበር እና ከሌሎች ህገወጥ ተግባራት መጠበቅን ያካትታሉ። |
|
ምርምሮችን እና የዳሰሳ ጥናቶችን ለማካሄድ። ለምሳሌ፣ የእርስዎን አስተያየት ለመጠየቅ ተጠቃሚዎቻችንን ስናነጋግር። |
ሕጋዊ ፍላጎት እዚህ ላይ ያሉት ሕጋዊ ፍላጎቶቻችን ተጠቃሚዎች ስለSpotify አገልግሎቱ እንዴት እንደሚያስቡ እና እንዴት እንደሚጠቀሙበት የበለጠ መረዳትን ያካትታል። |
|
ሕጋዊ መብቶች ወስጥ ሕጋዊ ፍላጎቶች እንደ ሕጋዊ መሰረት በማይታወቁበት፣ ስልጣኖች፣ በውል አስፈላጊነት ወይም ፈቃደኝነት ላይ እንመካለን።
5. የግል ውሂብዎን ማጋራት
ይህ ክፍል በእርስዎ የSpotify አገልግሎት አጠቃቀም በኩል የተሰበሰበ ወይም የመነጨውን የግል ውሂብ ማን እንደሚቀበል ይገልጻል።
በይፋ የሚገኝ መረጃ
የሚከተለው የግል ውሂብ ሁልጊዜ በSpotify አገልግሎት ላይ በይፋ ይገኛል (ካገዱት ማንኛውም ተጠቃሚ በስተቀር)፦
- የመገለጫ ስምዎ
- የመገለጫ ፎቶዎ
- የእርስዎ ይፋዊ አጫዋች ዝርዝሮች
- በSpotify አገልግሎት ላይ የሚለጥፋቸው ሌሎች ይዘቶች፣ እና ማንኛውም ተዛማጅ ርዕሶች፣ መግለጫዎች እና ምስሎች
- በSpotify አገልግሎት ላይ ማንን እንደሚከተሉ
- በSpotify አገልግሎት ላይ ማን እንደሚከተልዎት
እርስዎ ወይም ሌላ ተጠቃሚ እንደ ማህበራዊ ሚዲያ ወይም የመልእክት መላላኪያ መድረኮች ባሉ የሦስተኛ ወገን አገልግሎቶች ላይ የተወሰነ መረጃ ማጋራት ይችላሉ። ይህ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
- የእርስዎ መገለጫ
- በSpotify ላይ የሚለጥፉት ማንኛውም ይዘት እና ስለይዘቱ ዝርዝሮች
- የእርስዎ አጫዋች ዝርዝሮች እና ማንኛውም ተዛማጅ ርዕሶች፣ መግለጫዎች እና ምስሎች
ይህ መጋራት ሲከሰት፣ የሦስተኛ ወገን አገልግሎት የእነሱን ባህሪያት ለመደገፍ ቅጂውን ሊያከማች ይችላል።
ለማጋራት ሊመርጧቸው የሚችሏቸው የውሂብ ምድቦች
የሚከተለውን የግል መረጃ ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ላይ ከተዘረዘሩት ጋር ብቻ እናጋራለን።
- የSpotify አገልግሎት ባህሪን ወይም የሦስተኛ ወገን የመተግበሪያ አገልግሎትን ወይም መሣሪያን ለመጠቀም ከመረጡ እና ይህን ለማንቃት የግል ውሂብን ማጋራት አለብን፣ ወይም
- አለበለዚያ የግል ውሂቡን እንድናጋራ ፈቃድ ከሰጡን። ለምሳሌ፣ በSpotify አገልግሎት ውስጥ ተገቢውን ቅንብር በመምረጥ ወይም ፈቃደኝነትዎን በመስጠት ሊያደርጉት ይችላሉ።
የተቀባይ ምድቦች
|
ለማጋራት መምረጥ የሚችሏቸው የውሂብ ምድቦች
|
የማጋራት ምክንያት
|
---|---|---|
ከSpotify መለያዎ ጋር የሚያገናኟቸው የሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎች፣ አገልግሎቶች እና መሣሪያዎች |
|
የSpotify መለያዎን ለማገናኘት ወይም የSpotify አገልግሎትን ከሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎች፣ አገልግሎቶች ወይም መሣሪያዎች ጋር ተገናኝቶ መጠቀም እንዲችሉ። የእነዚህ የሦስተኛ ወገን መተግበሪያዎች፣ አገልግሎቶች እና መሣሪያዎች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
ብዙ የሦስተኛ ወገን ግንኙነቶችን በመለያዎ ውስጥ በ«መተግበሪያዎች» ስር ማየት እና ማስወገድ ይችላሉ። |
የድጋፍ ማህበረሰብ |
|
የSpotify ድጋፍ ማህበረሰብ አገልግሎትን እንዲጠቀሙ ለማስቻል። በSpotify ድጋፍ ማህበረሰብ ላይ ለመለያ ሲመዘገቡ፣ የመገለጫ ስም እንዲፈጥሩ እንጠይቅዎታለን። ይህ የSpotify ድጋፍ ማህበረሰብን ለሚጠቀም ማንኛውም ሰው በይፋ ይታያል። እርስዎ የሚለጥፏቸውን ጥያቄዎች ወይም አስተያየቶች እናሳያለን። |
ሌሎች የSpotify ተጠቃሚዎች |
|
ስለ እርስዎ የSpotify አገልግሎት አጠቃቀም መረጃ ለሌሎች የSpotify ተጠቃሚዎች ለማጋራት። እነዚህ በSpotify ላይ ያሉ ተከታዮችዎን ሊያካትቱ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ በ« ማህበራዊ » ቅንብሮች ስር በቅርብ የተጫወቱትን የእርስዎን አርቲስቶች እና የአጫዋች ዝርዝሮች በመገለጫዎ ላይ ለማጋራት መምረጥ ይችላሉ። እንዲሁም ከሌሎች ተጠቃሚዎች ጋር የተጋራ አጫዋች ዝርዝር ለመፍጠር ወይም ለመቀላቀል መምረጥ ይችላሉ። የተጋሩ አጫዋች ዝርዝሮች በማዳመጥ ተግባርዎ ላይ በመመስረት ማህበራዊ ጥቆማዎችን ይሰጡዎታል። |
አርቲስቶች እና የመዝገብ መለያዎች |
|
ከአርቲስቶች፣ ከመዝገብ መለያዎች ወይም ከሌሎች አጋሮች ዜና ወይም የማስተዋወቂያ ቅናሾችን ለመቀበል። ለዚህ ዓላማ የእርስዎን የተጠቃሚ ውሂብ ለማጋራት መምረጥ ይችላሉ። ሁልጊዜ ሃሳብዎን ለመቀየር እና የእርስዎን ፈቃደኝነት በማንኛውም ጊዜ የመሰረዝ አማራጭ ይኖርዎታል። |
ልናጋራው የምንችለው መረጃ
ለማን እና ለምን እንደምናጋራ ዝርዝሮችን ለማግኘት ይህን ሰንጠረዥ ይመልከቱ።
የተቀባይ ምድቦች
|
የውሂብ ምድቦች
|
የማጋራት ምክንያት
|
---|---|---|
አገልግሎት አቅራቢዎች |
|
ስለዚህ አገልግሎቶቻቸውን ለSpotify ማቅረብ ይችላሉ። እነዚህ አገልግሎት አቅራቢዎች የሚከተሉትን ለማድረግ የምንቀጥራቸውን ያካትታሉ፦
|
የክፍያ አጋሮች |
|
ስለዚህ ክፍያዎችዎን እና የጸረ-ማጭበርበር ዓላማዎችን ማስሄድ ይችላሉ። |
የማስታወቂያ አጋሮች |
|
ስለዚህ በSpotify አገልግሎት ላይ ይበልጥ ተዛማጅነት ያለው ማስታወቂያ ለእርስዎ እንድናደርስ እና የማስታወቂያዎችን ውጤታማነት ለመለካት ሊረዱን ይችላሉ። ለምሳሌ፣ የማስታወቂያ አጋሮቻችን የተስማሙ ማስታወቂያዎችን ለማመቻቸት ያግዙናል። |
የግብይት አጋሮች |
|
Spotifyን ለአጋሮቻችን ለማስተዋወቅ። ለሚከተሉት ምክንያቶች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የተወሰነ የተጠቃሚ ውሂብን እና የአጠቃቀም ውሂብን ለእነዚህ አጋሮች እናካፍላለን፦
የአጋሮች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
አጋሮቻችን ለእነሱ የምንጋራውን የግል ውሂብ ስለእርስዎ ከሚሰበስቡ ከሌሎች መረጃዎች ጋር ሊያጣምሩት ይችላሉ፣ ለምሳሌ፣ የእርስዎ የእነሱን አገልግሎቶች አጠቃቀም። እኛ እና አጋሮቻችን ይህን መረጃ ለእርስዎ አቅርቦቶችን፣ ማስተዋወቂያዎችን ወይም ሌላ ለእርስዎ አግባብነት አላው ብለን የምናስበውን ግብይት ለማቅረብ ልንጠቀም እንችላለን። |
አዘጋጅ መድረኮች |
|
አዘጋጅ መድረኮች ለእርስዎ ማድረስ እንዲችሉ ፖድካስቶችን ያዘጋጃሉ። ፖድካስት ሲያጫውቱ እንደ አይፒ አድራሻዎ ያሉ አንዳንድ መረጃዎችን ለአዘጋጅ መድረኮች እናጋራለን። እንዲሁም ባለቤትነታቸው የSpotify ያልሆነ ለሌሎች አዘጋጅ መድረኮች የሚገኙ ፖድካስቶችን በዥረት እንዲለቁ እንፈቅዳለን። የፖድካስት አቅራቢዎች የትኛው መድረክ ፖድካስቱን እያዘጋጀ እንደሆነ በትርዒት ወይም በክፍል መግለጫው ላይ ማብራራት አለባቸው። ለእነሱ የተጋራውን ውሂብ እንዴት እንደሚጠቀሙ ለማወቅ የአዘጋጁ መድረኩን የራሱን የግላዊነት መመሪያ ይመልከቱ። |
ትምህርታዊ ተመራማሪዎች |
|
እንደ ስታቲስቲካዊ ትንተና እና ትምህርታዊ ጥናት ላሉት ተግባራት፣ ነገር ግን ለዪ መረጃው በተደበቀ ቅርጸት ብቻ። ለዪ መረጃው የተደበቀ ውሂብ ማለት የእርስዎ ውሂብ ከእርስዎ ስም ወይም ሌላ በቀጥታ በሚለይ መረጃ ሳይሆን በኮድ የሚታወቀው ማለት ነው። |
Spotify የገዛቸው ኩባንያዎችን ጨምሮ ሌሎች የSpotify ቡድን ኩባንያዎች |
|
የዕለት ተእለት የንግድ ክወናዎቻችንን ለማከናወን እና የSpotify አገልግሎትን እና የተገዙ ኩባንያዎች አገልግሎቶችን ለመጠበቅ፣ ለማሻሻል እና ለማቅረብ እንድንችል። ለምሳሌ፦
|
የሕግ አስከባሪ አካላት እና ሌሎች ባለሥልጣናት ወይም ሌሎች ሕጋዊ እርምጃ የሚወስዱ አካላት |
|
በቅን እምነት ስናምን ይህን ማድረግ ለእኛ አስፈላጊ ነው፣ ለምሳሌ፦
|
የንግዳችን ገዢዎች |
|
ንግዳችንን ለገዥ ወይም ገዢ ሊሆን ለሚችል ልንሸጥ ወይም ልንደራደር ቢሆን። በዚህ ሁኔታ፣ እንደ የግብይቱ አካል የእርስዎን የግል ውሂብ ወደ ተተኪ ወይም አጋር ልናስተላልፍ እንችላለን። |
6. የውሂብ ማቆየት
የSpotify አገልግሎትን ለእርስዎ ለማቅረብ እና ለSpotify ሕጋዊ እና አስፈላጊ የንግድ ዓላማዎች አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ የእርስዎን የግል ውሂብ እናቆያለን፣ ለምሳሌ፦
- የSpotify አገልግሎትን አፈጻጸም መጠበቅ
- ስለ አዳዲስ ባህሪያት እና አቅርቦቶች በውሂብ ላይ የተመሰረቱ የንግድ ውሳኔዎችን መወሰን
- ሕጋዊ ግዴታዎቻችንን ማክበር
- አለመግባባቶችን መፍታት
አንዳንዶቹ የእኛ ይዞ የማቆያ ጊዜያት ምድቦች እና እነሱን ለመወሰን የምንጠቀምባቸው መስፈርቶች እነሆ፦
- እስከሚያስወግዱት ድረስ ውሂብ ተይዞ ይቆያል
የተወሰነ የግል ውሂብዎን እንድንሰርዝ መጠየቅ መብትዎ ነው። ለተጨማሪ መረጃ እና በጥያቄዎ መሰረት እርምጃ ልንወስድባቸው ስለምንችልባቸው ሁኔታዎች <<የእርስዎ የግል ውሂብ መብቶች እና መቆጣጠሪያዎች>> ክፍል 2ውስጥ ያለውን <<መደምሰስ>> የሚለውን ክፍል ይመልከቱ።
እንዲሁም የተወሰነ የግል ውሂብዎን በቀጥታ ከSpotify አገልግሎት ማጥፋት ይችላሉ፦ ለምሳሌ፣ የመገለጫ ሥዕልዎን ማርትዕ ወይም ማጥፋት ይችላሉ። ተጠቃሚዎች የግል ውሂቡን በራሳቸው ማየት እና ማዘመን በሚችሉበት ቦታ ላይ ከታች ከተገለጹት የተወሰኑ ዓላማዎች ውስጥ አንዱ ካልተተገበረ በስተቀር ተጠቃሚው እስከመረጡት ድረስ መረጃውን እናቆየዋለን። - ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ጊዜው የሚያልፍበት ውሂብ
አንዳንድ ውሂቦች ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ጊዜያቸው እንዲያልፍባቸው የተወሰኑ ይዞ የማቆያ ጊዜዎችን አቀናብረናል። ለምሳሌ፣ እንደ የፍለጋ መጠይቆች አካል ሊያስገቡት የሚችሉት የግል ውሂብ በአጠቃላይ ከ90 ቀናት በኋላ ይጠፋል። - የSpotify መለያዎ እስኪሰረዝ ድረስ ውሂብ ተጠብቆ ይቆያል
የSpotify መለያዎ እስኪጠፋ ድረስ አንዳንድ ውሂብ እናስቀምጣለን። የዚህ ምሳሌዎች የእርስዎን የSpotify የተጠቃሚ ስም እና የመገለጫ መረጃ ያካትታሉ። እንዲሁም በተለምዶ ለመለያው ሕይወት በዥረት የመልቀቅ ታሪክን እናቆያለን፣ ለምሳሌ፣ ተጠቃሚዎች የሚደሰቱባቸው የመልሶ ምልከታ አጫዋች ዝርዝሮችን እና የማዳመጥ ልማዶችን ከግምት ውስጥ የሚያስገቡ ግላዊነት የተላበሱ ጥቆማዎችን (ለምሳሌ፣ የእርስዎ የሰዓት እንክብል ወይም የእርስዎ በጋ ላይ ያዳመጡት) ለማቅረብ። የSpotify መለያዎ ሲሰረዝ፣ ይህ የውሂብ ምድብ ይጠፋል ወይም የማይለይ ይሆናል። - ለተወሰኑ ዓላማዎች ለረጅም ጊዜ ተይዞ ሚቆይ ውሂብ
መለያዎ ከተሰረዘ በኋላ፣ አንዳንድ ውሂብን ረዘም ላለ ጊዜ እናቆየዋለን ነገር ግን በጣም ውስን ለሆኑ ዓላማዎች። ለምሳሌ፣ ይህን ለሚጠይቁ የሕግ ወይም የውል ግዴታዎች ተገዢ ልንሆን እንችላለን። እነዚህ የግዴታ የውሂብ ይዞ የማቆየት ሕጎችን፣ ከምርመራ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ውሂቦች ለመጠበቅ ያሉ የመንግሥት ትዕዛዞችን ወይም ለፍርድ ቤት ሙግቶች የተቀመጡ ውሂቦችን ያካትታሉ። እንዲሁም ለተወሰነ ጊዜ ያህል ከSpotify አገልግሎት የተወገደ ውሂብን ልናቆይ እንችላለን። ይህም ሊሆን የሚችለው፦- የተጠቃሚ ደህንነትን በማረጋገጥ ለማገዝ ወይም
- በመድረካችን ላይ ካሉ ጎጂ ይዘቶች ለመጠበቅ።
ይህ በተጨማሪ የእኛን የተጠቃሚ መመሪያዎች እና የመድረክ ደንቦች ሊጥሱ የሚችሉ ነገሮችን እንድንመረምር ያግዘናል። በሌላ መልኩ፣ ሕጉ እንድናደርግ የሚያስገድደን ከሆነ ሕገወጥ የሆነ ይዘትን እናስወግዳለን።
7. ወደ ሌሎች አገራት ማስተላለፍ
በንግዳችን ዓለም አቀፍ ባህሪ ምክንያት፣ Spotify የSpotify አገልግሎትን ለእርስዎ ለማቅረብ የግል ውሂብን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ለSpotify ቡድን ኩባንያዎች፣ ለንዑስ ሥራ ተቋራጮች እና ለአጋሮች ያጋራል። የውሂብ ጥበቃ ሕጎቻቸው እንደ አውሮፓ ህብረት ሕጎች ወይም እርስዎ በሚኖሩበት ቦታ ላይ ተፈጻሚ እንደሆኑ ሕጎች ጠንካራ ተደርገው በማይቆጠሩ ሃገራት ውስጥ የእርስዎን ውሂብ ሊያሰናዱ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ በውሂብዎ ላይ ተመሳሳይ መብቶችን ላይሰጡዎት ይችላሉ።
የግል ውሂብን በዓለም አቀፍ ደረጃ በምናስተላልፍበት ጊዜ፣ መሣሪያዎችን የሚከተሉትን ነገሮች ለማድረግ እንጠቀማለን፦
- የውሂብ ማስተላለፉ የሚመለከተውን ህግ እንደሚያክብር ለማረጋገጥ
- ለውሂብዎ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ካለው ጋር ተመሳሳይ የጥበቃ ደረጃ ለመስጠት ለማገዝ
እያንዳንዱ የውሂብ ማስተላለፍ የሚመለከተውን የአውሮፓ ህብረት ህግ እንደሚያከብር ለማረጋገጥ የሚከተሉትን የሕግ ዘዴዎችን እንጠቀማለን፦
- መደበኛ የውል አንቀጾች (<< ኤስሲሲዎች >>)። እነዚህ አንቀጾች ሌላኛው ወገን የእርስዎን ውሂብ እንዲጠብቅ እና በአውሮፓ ህብረት ደረጃ መብቶች እና ጥበቃዎችን እንዲሰጥዎት ያስገድዳሉ። ለምሳሌ፣ በክፍል 3 << ስለእርስዎ የምንሰበስበው የግል መረጃ >> ላይ የተገለጸውን የግል ውሂብ በአሜሪካ ውስጥ አገልጋዮችን ለሚጠቀም አዘጋጅ አቅራቢችን ለማስተላለፍ ኤስሲሲዎችን እንጠቀማለን። እኛን ወይም የእርስዎን የግል ወሂብ የሚያስሄደውን ሦስተኛ ወገን በማነጋገር በመደበኛ የውል አንቀጾች መሰረት መብቶችዎን መጠቀም ይችላሉ።
- የበቂነት ውሳኔዎች። ይህ ማለት በአውሮፓ ኮሚሽኑ እንደተወሰነው የግል ውሂብን ለመጠበቅ በቂ ሕጎች ላሏቸው ከአውሮፓ ኢኮኖሚያዊ አካባቢ ውጭ ወደሆኑ አገሮች የግል ውሂብን እናስተላልፋለን ማለት ነው። ለምሳሌ፣ በክፍል 3 << ስለእርስዎ የምንሰበስበው የግል መረጃ >> ላይ የተገለጸውን የግል ውሂብ በዩናይትድ ኪንግደም፣ በካናዳ፣ በጃፓን፣ በኮሪያ ሪፐብሊክ እና በስዊዘርላንድ ለሚገኙ ሻጮች እናስተላልፋለን።
ለእያንዳንዱ የውሂብ ማስተላለፍ እንደ ተገቢነቱ ተጨማሪ ጥበቃዎችን ለይተን እንጠቀማለን። ለምሳሌ፣ የሚከተሉትን እንጠቀማለን፦
- እንደ ምስጠራ እና ለዪ መረጃ መደበቅ ያሉ ቴክኒካዊ ጥበቃዎች
- ተመጣጣኝ ያልሆነ ወይም ሕገወጥ የመንግስት ስልጣን ጥያቄዎችን ለመቃወም ፖሊሲዎች እና ሂደቶች
8. የግል ውሂብዎን ደህንነት መጠበቅ
የተጠቃሚዎቻችንን የግል ውሂብ ለመጠበቅ ቁርጠኞች ነን። የግል ውሂብዎን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያግዙ ተገቢ የሆነ ቴክኒካዊ እና ድርጅታዊ እርምጃዎችን አዘጋጅተናል። ሆኖም፣ የትኛውም ስርዓት ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዳልሆነ ልብ ይበሉ።
በስርዓታችን ውስጥ ያልተፈቀደ መዳረሻን እና አላስፈላጊ የግል ውሂብን ይዞ ማቆየትን ለመከላከል የተለያዩ መከላከያዎችን አስቀምጠናል። እነዚህ ለዪ መረጃን መደበቅ፣ ምስጠራ፣ መዳረሻ እና ይዞ የማቆየት መመሪያዎችን ያካትታሉ።
የተጠቃሚ መለያዎን ለመጠበቅ፣ የሚከተሉትን እንዲያደርጉ እናበረታታዎታለን፦
- ለSpotify መለያዎ እርስዎ ብቻ የሚጠቀሙትን ጠንካራ የይለፍ ቃል ይጠቀሙ
- የይለፍ ቃልዎን ለማንም ሰው በጭራሽ አያጋሩ
- የኮምፒውተርዎን እና የአሳሽዎን መዳረሻ ይገድቡ
- የSpotify አገልግሎቱን በተጋራ መሣሪያ ላይ መጠቀመዎን እንደጨረሱ እንደጨረሱ ይውጡ
- መለያዎን ስለመጠበቅየበለጠ ያንብቡ
በመለያ ገጽዎ ላይ<< ከሁሉም ቦታ ዘግተህ ውጣ >> የሚለውን ተግባር በመጠቀም ከብዙ ቦታዎች ከSpotify በአንድ ጊዜ መውጣት ይችላሉ።
ሌሎች ግለሰቦች የSpotify መለያዎ መዳረሻ ካላቸው፣ ከዚያ በመለያዎ ውስጥ የሚገኘውን የግል ውሂብ፣ መቆጣጠሪያዎችን እና የSpotify አገልግሎትን መድረስ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ምናልባት አንድ ሰው የእርስዎን መለያ በተጋራ መሣሪያ ላይ እንዲጠቀም ፈቅደው ይሆናል።
ይህን የግል ውሂብ ለእነሱ ቢያጋሩ ቅር ለማይልዎት ግለሰቦች ብቻ መለያዎን እንዲጠቀሙ መፍቀድ የእርስዎ ኃላፊነት ነው። የSpotify መለያዎን ሌላ ሰው መጠቀሙ ግላዊነት የተላበሱ ጥቆማዎችዎ ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር እና በውሂብ ማውረድዎ ውስጥ ሊካተት ይችላል።
9. ልጆች
ማስታወሻ፦ ይህ መመሪያ የSpotify ልጆች የግላዊነት መመሪያ ካላለ ድረስ በSpotify ልጆች ላይ አይተገበርም። Spotify ልጆች የተለየ የSpotify መተግበሪያ ነው።
የSpotify አገልግሎት በእያንዳንዱ ሀገር ወይም ክልል ውስጥ አነስተኛ << የእድሜ ገደብ >> አለው። የSpotify አገልግሎት ዕድሜያቸው የሚከተለው ለሆኑ ህጻናት አይመራም፦
- ዕድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ፣ ወይም
- ዕድሜያቸው የግል ውሂባቸውን ለማሰናዳት ህገወጥ የሚያደርግ፣ ወይም
- ዕድሜያቸው የግል ውሂባቸውን ለማሰናዳት የወላጅ ፈቃድ የሚፈልግ
ከሚመለከተው የዕድሜ ገደብ በታች ከሆኑ ልጆች የግል ውሂብን እያወቅን አንሰበስብም ወይም አንጠቀምም። ከእድሜ ገደብ በታች ከሆኑ የSpotify አገልግሎን አይጠቀሙ እና ለእኛ ምንም አይነት የግል ውሂብ አያቅርቡ። በምትኩ፣ የSpotify Kidsመለያ እንዲጠቀሙ እንመክራለን።
ከእድሜ ገደብ በታች ለሆነ ልጅ ወላጅ ከሆኑ እና ልጅዎ ለSpotify የግል ውሂብ እንዳቀረበ ካወቁ፣ እኛን ያነጋግሩን።
በሚመለከተው የዕድሜ ገደብ በታች ከሆኑ ልጅ የግል ውሂብ እንደሰበሰብን ከተረዳን የግል ውሂቡን ለመሰረዝ ምክንያታዊ እርምጃዎችን እንወስዳለን። ይህ የዚያን ልጅ የSpotify መለያ እንድንሰርዝ ሊያገድደን ይችላል።
በዋናው የSpotify አገልግሎት ላይ የጋራ መሣሪያ ሲጠቀሙ፣ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ግለሰቦች ማንኛውንም አግባብነት የሌለው ይዘት ስለማጫወት ወይም ስለመጠቆም ይጠንቀቁ።
10. በዚህ መመሪያ ላይ የተደረጉ ለውጦች
አልፎ አልፎ በዚህ መመሪያ ላይ ለውጦችን ልናደርግ እንችላለን።
በዚህ መመሪያ ላይ ቁሳዊ ለውጦችን ስናደርግ፣ በሁኔታዎች ላይ እንደ አስፈላጊነቱ የሚታይ ማስታወቂያ ልናቀርብልዎ እንችላለን። ለምሳሌ፣ በSpotify አገልግሎት ውስጥ የሚታይ ማስታወቂያ ልናሳይ ወይም የኢሜይል ወይም የመሣሪያ ማሳወቂያ ልንልክልዎ እንችላለን።
11. እኛን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ
በዚህ መመሪያ ላይ ላሉ ማናቸውም ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች የእኛን የውሂብ ጥበቃ ኦፊሰር ከእነዚህ መንገዶች በአንዱን ያነጋግሩ፦
- privacy@spotify.com ላይ ኢሜይል ይላኩ
- በ፦ Spotify AB፣ Regeringsgatan 19፣ 111 53 Stockholm፣ Sweden ይጻፉልን
Spotify AB በዚህ መመሪያ ስር የሚሄድ የግል ውሂብ የውሂብ ተቆጣጣሪ ነው።
© Spotify AB