የደህንነት እና ግላዊነት ማዕከል

እንኳን ደህና መጡ

Spotify በዓለም ዙሪያ ካሉ ፈጣሪዎች በሚሊየኖች ለሚቆጠሩ ሙዚቃዎች እና ሌሎች ይዘት መዳረሻን የሚሰጥዎት የዲጂታል ሙዚቃ፣ ፖድካስት እና ኦዲዮ መጽሐፍ አገልግሎት ነው። ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ለማቅረብ እና የተጠቃሚዎቻችንን ግላዊነት ለመጠበቅ ቁርጠኞች ነን። ያን ጥረት ለመደገፍ ዓለም አቀፍ ቡድኖቻችን በSpotify ላይ ተጠቃሚዎችን ከጉዳት ለመጠበቅ፣ የውሂባቸውን ደህንነት መጠበቅን ለማገዝ እና ተሞክሮው ለሁሉም ሰው አስደሳች መሆኑን ለማረጋገጥ ሌት ተቀን ይሠራሉ።