ግላዊነት
የግል ውሂብዎን በመሰብሰብ ላይ
ስለ እርስዎ የምንሰበስበው የግል ውሂብ ምን እንደሆነ፣ እንዴት እንደምንሰበስበው እና ለምን እንደሚያስፈልግ መረዳትዎ ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው።
የእርስዎን የግል ውሂብ በሚከተሉት መንገዶች እንሰበስባለን፦
- ለSpotify አገልግሎት ሲመዘገቡ ወይም መለያዎን ሲያዘምኑ - የSpotify አገልግሎቱን መጠቀም እንዲችሉ የእርስዎን የSpotify መለያ ለመፍጠር የተወሰነ የግል ውሂብ እንሰበስባለን። ይህ በእኛ የግላዊነት መመሪያ ክፍል 3 ውስጥ በበለጠ ዝርዝር እንደተገለጸው የመገለጫ ስምዎን እና የኢሜይል አድራሻዎን ያካትታል።
- በSpotify አገልግሎት አጠቃቀምዎ በኩል - የSpotify አገልግሎትን ሲጠቀሙ ወይም ሲደርሱ ስለ ድርጊቶችዎ የግል ውሂብን እንሰበስባለን እና እናሰናዳለን። ይህ እርስዎ ያጫወቷቸውን ሙዚቃዎች እና የፈጠሯቸውን አጫዋች ዝርዝሮች ያካትታል። ይህ በእኛ የግላዊነት መመሪያ ክፍል 3 ውስጥ የተካተተው የአጠቃቀም ውሂብ ምድብ ነው።
- ሊሰጡን የመረጡት የግል ውሂብ - እንዲሁም ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጨማሪ የግል ውሂብ ሊያቀርቡልን ወይም የግል ውሂብ እንድንሰበስብ ፈቃድ ሊሰጡን ይችላሉ ለምሳሌ፣ ተጨማሪ ባህሪያትን ወይም ተግባራትን ለእርስዎ ለማቅረብ። እነዚህ በእኛ የግላዊነት መመሪያ ክፍል 3 ውስጥ የሚገኙትን የድምፅ ውሂብ፣ የክፍያ እና የግዢ ውሂብ እና የዳሰሳ ጥናት እና የምርምር ውሂብ ምድቦችን ሊያካትቱ ይችላሉ።
- ከሦስተኛ ወገን ምንጮች የምንቀበለው የግል ውሂብ - ሌላ አገልግሎት ተጠቅመው ለSpotify ከተመዘገቡ ወይም የSpotify መለያዎን ከሦስተኛ ወገን መተግበሪያ፣ አገልግሎት ወይም መሣሪያ ጋር ካገናኙ ውሂብዎን ከእነዚያ ሦስተኛ ወገኖች እንቀበላለን። እንዲሁም የእርስዎን ውሂብ ከቴክኒካዊ አገልግሎት አቅራቢዎች፣ የክፍያ አጋሮች እና የማስታወቂያ እና ግብይት አጋሮች ልንቀበል እንችላለን። ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት የግላዊነት መመሪያውን ክፍል 3 ይመልከቱ።