የደህንነት እና ግላዊነት ማዕከል

ግላዊነት

የግል ውሂብዎን መጠበቅ

የተጠቃሚዎቻችንን የግል ውሂብ ለመጠበቅ ቁርጠኞች ነን። የግል ውሂብዎን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያግዙ አግባብነት ያላቸው ቴክኒካዊ እና ድርጅታዊ እርምጃዎችን እንተገብራለን። ሆኖም፣ የትኛውም ሥርዓት መቼም ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዳልሆነ ልብ ይበሉ።

በስርዓታችን ውስጥ ያልተፈቀደ መዳረሻን እና አላስፈላጊ የግል ውሂብን ይዞ ማቆየትን ለመከላከል የተለያዩ መከላከያዎችን አስቀምጠናል። እነዚህ ለዪ መረጃን መደበቅ፣ ምስጠራ፣ መዳረሻ እና ይዞ የማቆየት መመሪያዎችን ያካትታሉ።

የተጠቃሚ መለያዎን ለመጠበቅ፣ የሚከተሉትን እንዲያደርጉ እናበረታታዎታለን፦

  • ለSpotify መለያዎ ብቻ የሚጠቀሙትን ጠንካራ የይለፍ ቃል ይጠቀሙ
  • የይለፍ ቃልዎን ለማንም ሰው በጭራሽ አያጋሩ
  • የኮምፒውተርዎን እና የአሳሽዎን መዳረሻ ይገድቡ
  • የSpotify አገልግሎቱን በተጋራ መሣሪያ ላይ መጠቀመዎን እንደጨረሱ እንደጨረሱ ይውጡ
  • ለመለያዎ ጥበቃ ስለማድረግ ተጨማሪ ዝርዝር ያንብቡ

ተጨማሪ ዝርዝር ለማግኘት የእኛን የግላዊነት መመሪያ ክፍል 8 ይመልከቱ።